ይህን ያውቃሉ?

Posted by Basha BIRU on Friday, January 29, 2010 Under: መዝናኛ/ከዚህም ከዚያም
*የመጀመሪያዋ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው አውሮፕላን ፓቴዝ ትባላለች::የመጣችውም ከፈረንሳይ በ1922 ሲሆን የዚች አውሮፕላን ገጣጣሚዋ አንድሬ ሜሬዝ የተባለ ፈረንሳዊ ነው::
*የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገጣጠመችው አውሮፕላን "ጸሃይ" ስትባል ይህን ስያሜ ያገኘችውም በአጼ ሃይለ ስላሴ ሴት ልጅ በልእልት ጸሃይ ሃ/ስላሴ ስም ነበር:: ነገር ግን ይህችን አውሮፕላን የገጣጠማት ጀርመናዊ አውሮፕላኗን ኢትዮጵያ አንድ በማለት ነበር የሰየሟት::
*በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን የተመሰረተው በ1927 የሃገር ፍቅር ማህበር በሚል ስም ነበር::
*ለመጀመሪያ ግዜ በሚኒልክ መልክ ታትመው የወጡት ገንዘቦች ስራ ላይ የዋሉት በ1886 አ.ም ነበር::
*የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዶክተር /ዶክተር ማርቲን/ እየተባሉ የሚጠሩት ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ ነበሩ::
*የመጀመሪያው የሃገራችን ሆስፒታል ስራውን የጀመረው መጋቢት 7 ቀን በ1890 አ.ም ሲሆን የሆስፒታሉም ስም ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ይባላል::

ምንጭ
ይኔት መጽሄት ቅጽ 1 ቁጥር 11 

In : መዝናኛ/ከዚህም ከዚያም 



If you are unable to see amharic fonts please download most common amharic fonts in downloads catagory or click here.

Make a Free Website with Yola.