የቁልቁለቱ ሃይል

Posted by Basha BIRU on Monday, January 25, 2010 Under: Poems
አንዱ ነገር ካንዱ እየተጋመደ
እየተዛመደ
እየተዋለደ
በመቆየት ብቻ ቀኑ እየረፈደ
አዲስ አዲስ ነገር እየተለመደ
ለሃይል እየበረደ
ጭምቱ እያበደ
ቁም ነገሩ ቀርቶ እየተቀለደ
በቁልቁለት ጉዞ ሁሉም ተጠመደ
ተያይዞ ነጎደ
እየተካካደ
ዳገት ላይ ሰው ጠፋ አቀበት ከበደ
ሁሉም በሸርተቴ ቁልቁለት ወረደ
ሰው ተዋረደ
ገንዘብ ተወደደ
በእምነቱ በፍቅሩ በክብሩ ነገደ
በቁልቁለቱ ሃይል እየተገደደ

በፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

In : Poems 



If you are unable to see amharic fonts please download most common amharic fonts in downloads catagory or click here.

Make a Free Website with Yola.