የእኛ ሰው በአሜሪካ በነቢይ መኮንን _ የተሳካላቸው ሰዎች

Posted by Basha BIRU on Thursday, April 22, 2010 Under: Litrature ... Fiction/others
በአሜሪካ የተሳካላቸው አበሾች አሉ
ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ የጥቁር ጠይም ደንደን አጠር ያለ በምንም ጉዳይ ላይ ይለው ነገር የማያጣ በጣም ተጫዋች ሲቀርቡት የማይከብድ የእውቀት ማህደር ነው ::
"ከየት መጣህ የት ደረስክ ስንባባል ውድ ጊዜህን እንዳላባክን ግለ -ታሪኬንና እድሜ ዘመኔን ከነሲቪዬ ታገኘዋለህ :: እንደውም ቆይ ኮምፒውተር ላይ ሳይኖር አይቀርም " ብሎ ወደ ኮምፒውተሩ ሰሌዳ ዞሮ ለአንድ አፍታ አትሞ "ይሄን ተረከበኝ ወንድሜ :: ከዚህ በተረፈ
ብትፈልግ በሀሳብ ወደካዛንቺስ ብትፈልግ ውቤ በረሀ ይዘኸኝ ልትሄድ ትችላለህ " አለኝ :: ያለኝን በራሴ መንገድ አደረግሁ ::
ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ የተወለደው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ነው .. መጋቢት 5 1935 በዜግነት ግን አሜሪካዊ ነው :: ከፒኔ ውድስ ጁኒየር ኮሌጅ በኤሊመንተሪ ኢጁኬሽን የባችለር ዲግሪውን አግኝቶ በትሪኒቲ ዩኒቨርሲቲ ራሽያኛና ጣሊያንኛ ቋንቋዎችን ተምሮ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ጄኔራል ስተዲስ አጥንቶ ሲያበቃ ኒውዮርክ ከሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በፊልም ጥናቶች directing track and scholarship/criticism track ማስትሬት ዲግሪ ወስድዋል ::
በመጨረሻም አሁን (በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1994) በሚያስተምርበት የሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ በዋሽንግተን ዲሲ በአፍሪካ ጥናቶች የዶክትሬት ዲግሪ እጩ ሆኖ ፈተናውን አልፎ የመጨረሻ ወረቀቱን አጠናቅቆ በማቅረብ ላይ ይገኛል :: ዛሬ በሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ በኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት የሬድዮ ቴሌቪዥንና ፊልም መምሪያ በሙሉ ፕሮፌሰርነት ይሰራል :: ይህን ዲፓርትመንት ያቋቋመው ራሱ ሲሆን እንደነ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደዚህ እንዲመጡ በማድረግ ቁልፍ ሚና ተጫውትዋል ::
ይህን ያህል ተምሮ ምን ሰርትዋል ? ምንስ ሆኖ አገልግልዋል ? ማለት መቼም ያባት ነው :: የሰራው ስራ ሲደረደር ያስደነግጣል :: አንዳንዶቻችን በእድሜያችን እዚህ ትግባ የማትባል ትንሽ ስራ ያስመዘገብን እንደሆነ የአለምን ሪኮርድ የሰበርን ይመስል ዘራፍ ማለትን እንደባህል ሰልጥነንበታልና እንደው የጨዋ ቢሆነን ፕሮፌሰር የሰራበትን ቦታና ሙያ ብደረድረው መልካም መሰለኝ ::

*የማስ ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂና የአፍሪካና 3ተኛው አለም የልማት ጽንሰ ሀሳብ ስፔሻሊስት ::
*በአሜሪካን አየር ሀይል ዲሲ ስኳድሮን ዋና ፓይለትና የኤሮኖቲክስ ኢንስትራክተር :: የሞሽን ፓክስቸርስና የቴለቪዥን መሀንዲሶች ማህበር የቀድሞው አባል :: የአፍሪካውያን የመላው አለም የፊልም ስራዎች የቪድዮግራፊክስ ፌዴሬሽን መስራችና የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ::
*የፓን አፍሪካን ሲኒስጽ ፌዴሬሽን አባል ::
*የዋሽንግተን ዲሲ የት /ርት ቦርድ የመገናኛ ብዙሀን አማካሪ ::
*የቀድሞ የፖዘቲቭ ኢንኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንት ::
*የሰምና ወርቅ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር ::
*በቡርኪና ፋሶ ኡጋዱጉ በሚገኘው የጥቁር ኢንስቲትዩት በሚባለው ተቋም ውስጥ የአለም አቀፍ የስራ አመራር አባል ::
*የፋና ፕሮዳክሽንስ ፕሬዚዳንት ::
*የወርልድ ስፔስ አማካሪ ::
*የሚግኖ ሎራን ኢኒስ ፎርድ ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት :: ሌላም ሳይጽፍ የተዋቸው መአት አሉ .....

In : Litrature ... Fiction/others 


Tags: ethiopian life in washington dc  የእኛ ሰው በአሜሪካ 

If you are unable to see amharic fonts please download most common amharic fonts in downloads catagory or click here.

Make a Free Website with Yola.