"ፈረንሳይ ሀገር ያጋጠመኝን አንድ ነገር ላጫውታቹ
" አልኩ :: ሁሉም ከየሀሳብ ጎጆዋቸው እየወጡ "እሺ " በሚል አይን አዩኝ
::
"ፈረንሳይ አገር አንድ ሎጋ ወጣት
ልጅ ምን ልታደርግ ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለህ ? እያለ አላስቆም አላስቀምጥ አለኝ :: በመጨረሻም እስቲ ቤትህን አሳየኝ ? ብዬ በተራዬ አላስቆም
አላስቀምጥ አልኩት ::
ሄድን :: ያጋጠመኝ ነገር እጢዬን ዱብ
ነው ያደረገው :: ይሄ የ 24 አመት
ወጣት በአይን ግምት 58 አመት የሚሆናት ፈረንሳዊት አሮጊት አግብቶ ነው የተቀመጠው ::ከፈረንሳይ እንዳይወጣ ጭምር ከአሮጊትዋ ጋር በፊርማ ታስሮ
ነው የሚኖረው :: የሚገርመው ለምን ይህ ሊሆን ቻለ
? ብዬ ስሜት በማይነካ ትሁት አማርኛ ጠየኩት ::
"ጠርዘው ወደ ሀገሬ ሊመልሱኝ ሲሉ ይህን ዘዴ
አገኘሁ አለኝ ::
"እሺ እንዴት ትግባባላቹ ? እንዴት ማች ታደርጋላቹ ? ብዬ ጠየኩት ::
ብዙ አፈረ ::ብዙ አቀረቀረ :: የሚገርማቹ የባልና ሚስቱ ኑሮዋቸው ሀዘን ላይ ነው
የጣለኝ :: የሱ ሀላፊነት -ጉዋደኞችዋ ማለትም እስከ 65 አመት ያሉ አሮጊቶች
ባልንጀሮቹዋ ሲመጡ
ሻይ ማፍላት ቡና ማፍላት ሲወጡ
እጃቸውን ይዞ መንገድ ማሻገር የየሳምንቱ የብዙ ቀናት ስራው ነው
::
የመጣሁት እውነቱን ለመንገርና ለመናደድ ነበር :: ይሄን የመከራ ኑሮ እየኖርክ
ለምን አገርህ አትመለስም አልኩኝ ብዬ ለመቆጣት ነበር
:: ጉዳዩ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ ::በሁኔታው ልቤ በጣም
ተነክትዋል :: "አሳዝነኸኛል "
አልኩት አሁንም የልቤን መሳሳትና የአንጀቴን መንሰቅሰቅ በሚያሳይ ስስ አንደበት
:: አይኖቼ ላይ እንባ ተንቸረፈፈ :: በኑሮው እንደማይደሰት ለማወቅ ምንም መናገር
አላስፈለገውም :: አላስፈለገኝምም
:: ለመሆኑ እንደው
በሆነ አጋጣሚ እንዴት እየኖርክ እንደሆነ ለቤተሰቦችህ ወይም ለቅርብ ጓደኛህ
ወደ ኢትዮጵያ ደብዳቤ ጽፈህ ታውቃለህ ?"
"በጭራሽ "
"ለምን ?"
"ይሄ ማፈሪያ ነገር ምኑ ይጻፋል
?"
"ብትጽፈው ጥሩ ነበር "
"ተወው ብትፈልግ አንተ ጻፈው :: ፈቃዱን ሰጥቸሀለሁ " አለኝ ከዚያች ቀን
ወዲህ ስለ ከአገር መቅረት አውርቶኝ አያውቅም ::
In : Litrature ... Fiction/others
Tags:
life in america
life in france
ኢትዮጵያዊ በፈረንሳይ