የኛ ሰው በአሜሪካ በነቢይ መኮንን ገጽ 16...
Posted by Basha BIRU on Thursday, April 22, 2010 Under: Litrature ... Fiction/others
ዋሺንግተን ዲሲ ዱከም ሬስቶራንት
ውስጥ ነው ውስጥ ነው ::
ለምንድነው የሚሰሩትን ስራ ለመግለጽ የማይፈልጉት ? ለምንድነው መማር የሁሉም ፍላጎት ያልሆነው ?ለምንድነው ከኢትዮጵያ በእንግድነት የመጣ ሰው እዚያ እንዲቀር የሚፈልጉት ? የት ሲሰሩ ውለው ነው ማታ ማታ አበሻ ሬስቶራንት የሚመጡት ?ብዙ ጥያቄዎች በአይምሮዬ ተመላለሱ ::ቀስ በቀስ መጋረጃውን ገልጬ ጽላቱን ማየቴ አይቀርም ብዬ ለሚስጥሩ ጊዜ ሰጠሁት ::በወቅቱ ራት ከሚጋብዙኝ ወዳጆቼ አንዱን "እስቲ በአጭሩ መልስልኝ "አሜሪካን ሀገር ስራ አይጠየቅም !" የሚባለው ለምንድነው ?"
"ይገርምሀል .. አለ ወዳጄ "እኔ ከአንድ ጉዋደኛዬ ጋር አንድ አመት ሙሉ ቤት ሼር አድርገን ኖረናል ::ግን እሱም እኔ ምን እንደምሰራ አያውቅም እኔም እሱ ምን እንደሚሰራ አላውቅም :: ግን እሱም የእሱ አይነት ስራ እንደምሰራ ይገምታል እኔም እንደሱ እገምታለሁ ::"
ወይ መልስ ?! አማርኛ ላለመግባቢያነት ሲያገለግል እንዲህ ነው ለካ ! ይኸው ነው የንግግራችን አጭሩ ትርጉም ::
የምታስተናግደን ኢትዮጵያዊት ልዩ ፈገግታ አላት ::በጣም ትሁት ናት :: እንዳጋጣሚ ሆኖ አንዲት ዘመድዋ ከእኛ አጠገብ ካለው ወንበር ላይ ከኔ አጠገብ ተቀምጣለች :: አልፎ አልፎ አስተናጋጅዋ እየመጣች ስለምታዋራት ወይ የዝምድና ወይ የወዳጅነት ወይ አንድ አይነት ቀረቤታ እንዳላቸው ያስታውቃል :: ሰላምታ ካቀረብኩ ቦሀላ "ምንሽ ናት ?" አልኩዋት አጠገባችን የተቀመጠችውን ልጅ ::
*የአክስቴ ልጅ
እዚህ ብዙ ግዜዋ ነው ?
*አይ ከካናዳ መጥታ ትንሽ ገንዘብ ልስራ ብላ ነው :: የስራ ልምዱን ሳትፈልገው አልቀረችም ::
ስንት ይከፍልዋታል ?
*ትንሽ የመገረም ሳቅ ፊትዋ ላይ እየታገለቻት በጥያቄ መለሰችልኝ "እንግዳ ነህ ?"
(በልቤ ደሞዝም አይጠየቅም ሊሉ ነው ወይስ በጣም ስለሚያንስ ያሳፍር ይሆን ? አልኩ )
የመጣሁት በቅርቡ ነው አልኩ ; ያ አሰልቺ ጥያቄ እንዳይመጣ እየፈራሁ (መቼ መጣህ ለምን መጣህ , ትመለሳለህ ?... የሚሉትን ነው
)
*እዚህ የሚሰሩ አስተናጋጆች በሙሉ ደሞዝ የላቸውም (በድንጋጤ አመዴ ቡን ነው ያለው )
ታድያ እንዴት ሊሆኑ ነው ? እንዴት ነው የሚኖሩት ?
*ቆይ እንደውም እራስዋ መጣችልህ እራስዋን ጠይቃት ::
እውነትም በፈገግታ እንደተሞላች አስተናጋጅዋ ወደ እኛ እየመጣች ናት ::"ውይ እህቴን አንቺን የመሰለች አበባ ለጋ ልጅ ካገርዋ ተሰዳ መጥታ ያለደሞዝ ትንገላታለች ...እናትዋ ...እህትዋ ....ሆ ብለው "እስዋ እንኩዋን ወደዲሲ አቀጠነች !" እያሉ የሸኝዋት አብሮ -አደግ ጉዋደኞችዋ ... ሁሉም እየታዩኝ በሀሳብ ነጎድኩ :: ጎረቤት ያለችው ልጅ ደግማ "በል ጠይቃታ ?" ስትለኝ ነው ወደዱከም የተመለስኩት ::
"እሺ " አልኩ በቀጥታ ወደጥያቄው ለመግባት አንደበቴ ሲሰንፍብኝ :: "እ " እያልኩ ሳመነታ :
"ምንድነው ልትጠይቀኝ የፈለከው ?"አልችኝ :: በፈገግታ አረፋ ውስጥ እንደምትናገር ሁሉ ነጫጮቹ ጥርሶችዋ ያበራሉ ::ይኩረፈረፋሉ ::
"ስንት ነው ደሞዝሽ ?" ፍርጥ አደረኩላት ::
"የምን ደሞዝ ?" ድምጽዋ ውስጥ "የማነህ ፋራ ?" የሚል ድምጽ ተሸብልቅዋል ::
"ታድያ በምን ገንዘብ ትኖሪያለሽ ?"
"በእናንተ ቲፕ .. እናንተ በምትሰጡኝ ጉርሻ ነዋ !" በድጋሚ ቀልቤ ተገፈፈ :: በዝምታ በረዶ ስር አቀርቅሬ "ዋ ህይወት !" አልኩኝ ::ሀዘን ልቤ ላይ ዳምንዋል ::ግን ፊቴ ላይ እንዳይታይብኝ በተቻለኝ እየተጣጣርኩ ነው :: የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በሰጠን ማህደር ውስጥ "አሜሪካኖች ዋጋ የሚሰጥዋቸው ሁለት ዋና ዋና ነገሮች 1.ትህትና የተላበሰ ሰው የመቀበል ባህሪ 2.የጉርሻ መስጠት ባህል "የሚል እንደነበረበት አስታወስኩ ::በስራ ተተርጉሞ እያየሁት ነው ማለት ነው እንዴ ? አልኩኝ ለራሴ ::ልጅትዋ እቃ እያነሳሳች ነው ::ወደ ጎረቤቴ ልጅ ዘወር ብዬ ...
"ለምን ዝም ብላ ወደ አገርዋ አትሰደድም ?"አልኩ ::ለካ እቃ እያነሳሳች ታዳምጥ ኖሮ መልስዋን በጥያቄ ሰጥታኝ ሄደች ::
"ደሞ ወደገዛ ሀገራችን መሰደድ ብሎ ነገር አለ እንዴ ?"
አጠገቤ ያሉ ጉዋደኞቼ እስኪገረሙ ድረስ ተመስጦዬ ውስጥ ተቀብሬ ብዙ ግዜ ቆዘምኩ ::

In : Litrature ... Fiction/others
Tags: life in america የእኛ ሰው በአሜሪካ